ONE BIBLE TRUTH /የእወነት ቃል /
ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን

ማደሪያዎችህ

ማደሪያዎችህ (Maderiyawocheh) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

አዝ፦ 
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

ክቡር ፡ ድንጋዮች ፡ ሕያዋን ፡ ልጆች
በበጉ ፡ ደም ፡ የተዋጁ ፡ ሰዎች
ቤተ ፡ መቅደስ ፡ ለመሆን ፡ ታነጹ
ማደሪያ ፡ ሆኑለት ፡ ለንጉሡ

አዝ፦ 
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

በዓለም ፡ አዕላፍ ፡ ዕርካታን ፡ ያጡ
ዝናህን ፡ ሰምተው ፡ ከሩቅ ፡ የመጡ
በኃጥአን ፡ ድንኳን ፡ ከሚቀመጡ
በአንተ ፡ ማደሪያ ፡ መጣል ፡ መረጡ

አዝ፦ 
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

በጓዳዎችህ ፡ ክቡር ፡ ነገሮች
ተከምረዋል ፡ የሰማይ ፡ ሃብቶች
በመብራት ፡ በዘይትህም ፡ ቅባቶች
እጅግ ፡ ደመቁ ፡ የአንተ ፡ ልጆች

አዝ፦ 
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

ካህናቶችህ ፡ በመለከቶች
መዘምራን ፡ በዜማ ፡ ዕቃዎች
ባንድነት ፡ ቃና ፡ ወጣ ፡ ድምጻቸው
ከፍ ፡ አደረጉህ ፡ በምሥጋናቸው

አዝ፦ 
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

በዘለዓለማዊው ፡ ምሕረቱ
ልኡል ፡ ጐበኘን ፡ በቸርነቱ
ጌታ ፡ ለሕዝቡ ፡ ሰጠ ፡ ሞገሱን
የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ሞላ ፡ መቅደሱን

አዝ፦ 
ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ (የዮሐንስ ወንጌል 1;12) This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free