በቅድሚያ “ልዩ ወንጌል” የተባለውምንድነው? ስለ ልዩ ወንጌል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥበገላትያ 1፡6 ላይ “በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት


እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤” ተብሎ ተጽፏል፡፡እንደዚሁም በ2ኛ ቆሮንቶስ 11፡4 ላይ “የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም
ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትንልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።”ተብሎ ተጽፏል፡፡ ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የምንረዳው ልዩ ወንጌል ተብሎ የተገለጸው
ከእውነተኛውና የሚያድነውን የምሥራች ከያዘው ወንጌል በተቃራኒ የሚገኝና እውነተኛውን ወንጌል ለማስተባበል የሚሰበክና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እውነተኛውን ወንጌል የሚቃወም መልእክት ነው፡፡ እንዲህ ያለው የተሳሳተ“ልዩ ወንጌል” በሚያጋጥመን ጊዜ እንዳንቀበለውና
በመልካም እንድንታገሰው ሐዋርያው ጳውሎስ በሁለቱም ጥቅሶች ውስጥ አስተምሮናል፡፡
እውነተኛው ወንጌል ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገርና መዳን በእርሱ በኩል ብቻ እንደሚገኝ የሚመሰክር ነው፡፡ ወንጌል ከዚህ ውጪ ሌላ መልእክት የለውም፡፡ ይህን ሐቅ ክዶ በሌላ ወገን ወይም በሌላ መንገድ መዳን እንደሚገኝ የሚሰብክ ሌላ መጽሐፍ ወይም ሰው ቢኖር መጽሐፉ ልዩ ወንጌል ሰውየውም የሐሰት አስተማሪ ነውና ሁለቱም የተወገዙ
ናቸው፡፡ ምክንያቱም “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።” ይላልና የእግዚአብሔር ቃል (ገላ. 1፡8-9)፡፡